የሀገር ውስጥ ዜና

የጅማ ዞን ለመከላከያ ሠራዊት ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

September 15, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ዞን ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የጅማ ዞን ነዋሪዎች ከዚህ ቀደምም ለሠራዊቱ ተመሳሳይ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ፥ የዛሬው ሁለተኛ ዙር መሆኑ ተመላክቷል።

የዞኑ ነዋሪዎች የሀገር ህልውናን ለማስከበር እየተዋደቁ ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት በ30 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የተደረገው ድጋፍ ከ500 በላይ ሰንጋ በሬዎችን እና ሌሎች ምግብ ነክ ግብዓቶችን ያካተተ መሆኑን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ትጃኒ ናስር ተናግረዋል፡፡

አስተዳዳሪው አሸባሪው ህወሓት ተደምስሶ የሀገር ሰላም እስኪረጋገጥ የዞኑ ነዋሪዎች የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በአሊዳን መሃመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!