የሀገር ውስጥ ዜና

በሐረሪ ክልል እህትማማቾች ውኃ ውስጥ ሰጥመው ሕይወታቸው አለፈ

By Mikias Ayele

September 14, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ድሬ ጠያራ ወረዳ ሁለት እህትማማች ሕጻናት በጉድጓድ ውስጥ ከተጠራቀመ ውኃ ለመቅዳት ሲሞክሩ ባጋጠማቸው አደጋ ሰጥመው ሕይወታቸው አልፏል፡፡

የድሬ ጠያራ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ እንደገለፁት÷ በወረዳው ገንደ ባላ ተብሎ በሚጠራ መንደር ውስጥ እህትማማቾቹ ለግብርና ሥራ ታስቦ ከተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ ውኃ ለመቅዳት ሲሞክሩ ሰጥመው ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ውኃ ለመቅዳት ሲሞክሩ አንደኛዋ ወደ ውኃ ጉድጓዱ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ሌላኛዋ የገባችውን ለማውጣት ስትሞክር ሁለቱም ጉድጓዱ ውስጥ መስጠማቸውን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚህ ወረዳ በተደጋጋሚ የሕጻናት ሕይወት በተመሳሳይ መልኩ እየጠፋ  በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አዛዡ አሳስበዋል፡፡