የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ያካሄደችው ሰፊ ማሻሻያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እያገኘ ነው- ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ

By Mikias Ayele

September 14, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ያካሄደችው ሰፊ ማሻሻያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እያገኘ ነው ሲሉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማሻሻል ባደረጉት ጥረት የ2022 የዓለም ኢስላሚክ የፋይናንስ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ “እንደ ሀገር ዘርፉን አካታች ለማድረግ ስለ ተጓዝናቸው ምዕራፎች ይህንን ሽልማት በመቀበሌ ክብር ይሰማኛል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዕድገትና መሻሻል ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነው ከዓለም አቀፉ ኢስላሚክ ፋይናንስ አመራር ሽልማቱ የተበረከተላቸው፡፡