Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደመቀ መኮንን በአውሮፓ ህብረት ከአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሪታ ላራንጂንሃ ጋር ተወያዩ።

በዚህ ወቅት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ስላለው ግጭት እና መንግስት እያደረገ ያለውን የሰላም ግንባታ ጥረት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላትን ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ያላትን ቁርጠኝነትም በዚህ ወቅት አረጋግጠዋል።

አቶ ደመቀ መንግስት በአፍሪካ ህብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ያለውን ቁርጠኝነት ጠቅሰው፥ የአውሮፓ ህብረትም ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ጉዳዮች ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሪታ ላራንጂንሃ በበኩላቸው፥ ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት ለማጠናከር ዝግጁ መሆኑን አንስተዋል።

አያይዘውም ህብረቱ በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት እንደሚደግፍ እና በየትኛውም ጊዜ የሰላም ሂደቱን ለመደገፍ ያለውን ዝግጁነት መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version