አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሬት ወረራና በፀጥታ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መሥራት እንዳለበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡
ከአዲስ አበባ የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመዲናዋ በተከናወኑ ሥራዎችና በሕዝብ ጥያቄዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ÷ በምገባ ስርዓት፣ ሰላምና ፀጥታን ለማሻሻል የሚደረገው ጥረት፣ የግንባታ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ የአካባቢ ፅዳትና ውበት አፈፃፀም ላይ አስተዳደሩ እያከናወነ ያለውን ሥራ አድንቀዋል፡፡
እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በኑሮ ውድነት፣ በግንባታ አቅርቦት፣ በመሬት ወረራ እና በፀጥታ ጉዳዮች ላይ አመራሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራ እንዳለበት አመላክተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፥ በየደረጃው ያለው አመራር እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በመውረድ ከሕዝቡ ጋር ተቀራርቦ እንዲሠራ ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ከነዋሪው ለተነሱ ጥያቄዎች በየደረጃው መልስ እየሰጠ ነው ማለታቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!