አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በጋራ ለመሥራት ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱን የፈረሙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጀማል አሕመድ ናቸው።
ወ/ሮ ሙፈሪሃት በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት÷ የሁለቱ ተቋማት ስምምነት በክህሎት እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ነው፡፡
“ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለበርካቶች የሥራ ዕድል የፈጠረ እና በሀገር ዕድገት ላይ ዐሻራውን እያኖረ ያለ ተቋም ነው” ማታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ከሚድሮክ ጋር በግብርና፣ ቱሪዝም እና ማዕድን በመሳሰሉ አምስት ዘርፎች የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማቅረብ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና የሙያ ደኅንነትን ለመጠበቅ በጋራ እንሠራለን ብለዋል፡፡
አቶ ጀማል አሕመድ በበኩላቸው÷ ሚድሮክ ያሉበትን የሥራ አመራር ክፍተት ለመሙላት በጋራ መሥራቱ መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል።