አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ ጃንፍራንኮ ሮቲግሊያኖ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ።
በምክክሩ ላይ ዪኒሴፍና አጋሮቹ በክልሉ እስካሁን ያደረጓቸውን ድጋፎች እና የሚታዩ ክፍተቶችን የሚያመላክት መነሻ ሠነድ ቀርቦ ተወያይተውበታል፡፡
አቶ አሻድሊ ሃሰን በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በክልሉ ተከስቶ በነበረው ግጭት የወደሙ ማህበራዊ ተቋማትን ወደ አገልግሎት ለመመለስና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ ዩኒሴፍና አጋሮቹ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል፡፡
ጃንፍራንኮ ሮቲግሊያኖ በበኩላቸው÷ ዩኒሴፍ እያደረገ ያለውን እገዛና ድጋፍ የበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!