የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በሴቶችና ወጣቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገውን ጉባኤ በንግግር ከፈቱ

By Shambel Mihret

September 12, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በታንዛኒያ ዳሬሰላም እየተካሄደ ባለው እና በሴቶች እና ወጣቶች ላይ ትኩረቱን ባደረገው ጉባኤ መክፈቻ ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

ጉባኤው በታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሐሰን እና በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሀፊ ዋምኬሌ ሜኔ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመርሐ ግብሩ የአፍሪካ ሀገራት የቀድሞ እና በአሁኑ ወቅት ኃላፊነት ላይ ያሉ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ተጋባዥ ሆነዋል።

በመክፈቻ መርሐ ግብሩም ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ  በበይነ −መረብ ለተሳታፊዎች መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፥ ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ቀናት ይቆያል።

ጉባኤው “ሴቶች እና ወጣቶች የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና  አንቀሳቃሽ  ናቸው”  በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ እንደሚገኝ ከታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡