የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች የኩፍኝ ክትባት እየተሰጠ ነው

By Melaku Gedif

September 12, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ደቡብ አሞ እና ኮንሶ ዞኖች የኩፍኝ በሽታ ክትባት እየተሰጠ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡

ክትባቱ የዓለም ጤና ድርጅት በኩፍኝ በሽታ ዙሪያ ከሚሰራው ሩቤላ ኢኒሼቲቭ ጋር በመተባበር ነው እየተሰጠ የሚገኘው፡፡

በዘመቻው ከክትባቱ በተጓዳኝ የዜጎች የተመጣጠነ ምግብ አወሳሰድ ሁኔታ ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡