አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዘንድሮ 2020 ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የ2020 አውሮፓ እግር ኳስ ዋንጫ ለ1 ዓመት እንዲራዘም ተወሰነ።
የዘንድሮ የአውሮፓ ዋንጫ በአውሮፓውያኑ ከሰኔ 2020 ጀምሮ ለአንድ ወር እንደሚካሄድ መርሃ ግብር ወጥቶ ነበር።
ሆኖም ግን በኮሮናቫይረስ ምክንያት የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ለ1 ዓመት እንዲራዘም የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በቴሌ ኮንፈረንስ ባካሄደው ውይይት መወሰኑን የኒርዌይ እግር ኳስ ማህበር አስታውቋል።
በዚህም መሰረት የአውሮፓ ዋንጫ በቀጣይ ዓመት ማለትም በአውሮፓውያኑ ከሰኔ እስከ ሀምሌ 2021 የሚካሄድ ይሆናል ነው የተባለው።
የአውሮፓ ዋንጫ መራዘም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተራዘሙ የሊግ ውድድሮች የማጠናቀቂያ እድሜ እንዲያገኙ የሚረዳ መሆኑንም የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ገልጿል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ