የሀገር ውስጥ ዜና

የሐረሪ ክልል ለ59 ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

By Feven Bishaw

September 09, 2022

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ59 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል፡፡

የክልሉ መንግስት ይቅርታ ያደረገው የይቅርታ መስፈርቱን አሟልተው ለተገኙ 59 ታራሚዎች መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡