አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 724 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ጣምያለው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በጤፍ፣ በበርበሬ እና በመድሃኒቶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 724 የንግድ ድርጅቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል።