ቢዝነስ

ከ13 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ

By Feven Bishaw

March 17, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ13 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ እና ሌሎች ግምታዊ ዋጋ ያልወጣላቸው የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር  የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ  ባለፉት ተከታታይ 12 ቀናት  በተለያየ የሀገሪቱ ክፍል  መያዙን አስታውቋል፡፡

እነዚህ ህገ-ወጥ እቃዎች ከባህር ዳር፣ ጅግጅጋ፣ መተማ፣ ኮምቦልቻ፣ ሀረር፣ አዋሽ፣ ቶጎ ውጫሌ፣ መቀሌ፣ አፋር ክልል ዞን 3 ዱለቻ ወረዳ፣ ምስራቅ ጉጂ ዞን ሻኪሶ ወረዳ እና በሌሎች የጉምሩክ ኬላ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ነው የተያዙት፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹም የጦር መሳሪያ፣ አልባሳት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የወርቅ ጌጣጌጥ፣ሺሻና መድኃኒቶች ፣ጊዜው ያለፈባቸው ምግቦችና ኤለክትሮኒክስ መሳሪያዎች ናቸው ፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ህጋዊ ሆነው ቀረጥ ከፍለው ምርቶችን ወደ አገር የሚያስገቡ ህጋዊ አስመጪዎች እንዲጎዱ እንደሚያደርግ መገለፁን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡