አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 3 ሚሊየን ብር የሚገመት የእርድ እንስሳት ድጋፍ አደረገ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደተናገሩት ፥ አሸባሪው ህወሓት ከመንግስት የቀረቡ የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው ሦስተኛ ዙር ጦርነት ከፍቷል ፡፡
ውድ ሕይወቱን በመክፈል ጦርነቱን እየመከተ የሚገኘውን የመከላከያ በስንቅ፣ በሞራልና በሰው ኃይል መደገፍ ወሳኝ መሆኑንም ነው የተናገሩት ፡፡
የክልሉ መንግስትም በመጀመሪያ ዙር ድጋፉ ሕዝቡን በማስተባበር 500 የፍየል ሙክቶች ድጋፍ አድርጓል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ ድጋፉፍ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ድጋፉም በክልሉ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተሰበሰበ መሆኑን መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በመርሐ-ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሃመድ ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።