የሀገር ውስጥ ዜና

የቲቢ ቤተ ሙከራ ማጠናከሪያ ፕሮጀክት ስብሰባውን እያካሄደ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

September 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ፣ መካከለኛው እና ደቡብ አፍሪካ የጤና ማህበረሰብ ግሎባል ፈንድ ክልላዊ የቲቢ ቤተ ሙከራ ማጠናከሪያ ፕሮጀክት 8ኛው የአስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው ስብሰባ በፕሮጀክቱ ላይ የሚታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን ለመገምገም ያለመ ነው፡፡