Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከተማ አስተዳደሩ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የተለያዩ የምግብ ነክና አልባሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ 191 ሰንጋዎች፣ 524 በግ፣ 287 ኩንታል በሶ፣ 151 ኩንታል ዳቦ ቆሎና 9 ሺህ 949 ጫማዎችን ያካተተ ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፥ ከሁለም ክፍለ ከተሞችና ከተለያዩ ተቋማት የተሰበሰበውን ድጋፍ ለብሔራዊ ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አስረክበዋል።

የመዲናዋ ነዋሪዎች አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለሁሉም ዜጎች ብሔራዊ ኩራት ለሆነውና ለሕይወቱ ሳይሳሳ ለሀገርና ለሕዝብ ደኅንነት እየተዋደቀ ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ማድረጋቸውንም ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል።

የብሔራዊ ሀብት አሰባሰብ ኮሚቴውን በመወከል ድጋፉን የተረከቡት የትራንስፖርት ሚኒስትርና የኮሚቴው ሰብሳቢ ዳግማዊት ሞገስ በበኩላቸው÷ የነዋሪዎች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ የሚደነቅና የሚያኮራ እንደሆነ መግለጻቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version