አዲስ አበባ፣ ጷጉሜን 2፣ 2014፣ (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን በ15 ሚሊየን ብር ወጪ ያስገነባቸውን 27 መኖሪያ ቤቶች እና ሥምንት የንግድ ሱቆች ለተጠቃሚዎች አስረከበ፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቤቶቹን ቁልፍ ለአቅመ ደካማ የከተማዋ ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት አስረክበዋል፡፡
አቶ ደበሌ÷ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ እናበሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ወገኖች የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በከተማዋ በተከናወኑት ሁለንተናዊ የማኅበራዊ አገልግሎቶች ከሚሽኑ ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆኑ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእውቅና ሽልማት እንደተበረከተለት ተጠቁሟል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ቁሳቁስ እና ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡