አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘’ለአምራችነት ስኬት የጋራ ጥረት ለሀገር እድገት’’ በሚል መሪ ሃሳብ የአምራችነት ቀን በሚሊኒየም አዳራሽ እየተከበረ ነው።
ግብርና ሚኒስቴር ፣ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ማዕድን ሚኒስቴር ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ፣ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በጋራ ያዘጋጁት የአምራችነት ቀን አውደ ርዕይ እና ባዛር በሚሊኒየም አዳራሽ ለታዳሚያን ክፍት ሆኖ እየተጎበኘ ነው።
አውደ ርዕዩን እና ባዛሩን የገንዘብ ሚኒስቴሩ አህመድ ሺዴ እና ሌሎች ሚኒስትሮች በጋራ ከፍተውታል።
በማህሌት ተክለብርሃን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!