Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በወሎ ግንባር ለተሰለፈው ጥምር ጦር ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የአይነት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር በወሎ ግንባር ለተሰለፈው ጥምር ጦር የእርድ ከብት እና በጎች ድጋፍ አደረገ፡፡
ለጥምር ጦሩ በከተማዋ ከሚገኙ አምስት ክፍለ ከተሞች የተሰበሰበ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በሚገመት ወጪ 13 የእርድ ከብቶቾ፣ 200 ፍየሎች እና መሰል ድጋፎች ተደርገዋል፡፡
የሰሜን ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ጋሻው አስማማው በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት የወገን ጦር ለሀገር ሰላም በግንባር እየተፋለመ እንደለ ሁሉ ደጀን ህዝብም አበረታች ስራዎችን እየሰራ ነው፡፡
በከተማ አስተዳደሩ ለጥምር ጦሩ የሚደረጉ መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተገልጿል፡፡
ለጥምር ጦሩ መንግስት እና ህዝብ በቅንጅት የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።
በለይኩን ዓለም
Exit mobile version