Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን ማዕከልን የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር፣ ጤና ሚኒስቴር እንዲሁም የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር በጥምረት በመሆን የጌርጌሴኖንን የአዕምሮ ሕሙማን ማዕከል ጎበኙ፡፡

ጉብኝቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶቹ እያከናወኑ የሚገኙት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አንዱ አካል መሆኑም ተመልክቷል፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ እና የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እንዲሁም የተቋማቱ ሰራተኞች መሳተፋቸውንም የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

ሦስቱ ተቋማት በድምሩ 450 ሺህ ብር በሚገመት ወጪ ለአዲስ ዓመት መዋያ የተለያዩ ስጦታዎች አበርክተዋል።

በተጨማሪ ሚኒስትሮቹ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ ደም የመለገስ መርሐ-ግብር ማካሄዳቸውም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version