የሀገር ውስጥ ዜና

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የበጎ ፈቃደኝነት ቀን በጋራ እያከበሩ ነው

By Meseret Awoke

September 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ፣ የትምህርት እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴሮች የበጎ ፈቃደኝነት ቀን በጋራ እያከበሩ ነው፡፡

ሚኒስቴሮቹ በጋራ የሚያዘግጁት የሙሉ ቀን መርሐ ግብር በሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እና የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት በተለያዩ ዝግጅቶች ተጀምሯል።

የትምህርት ተቋማትን ፅዱና ውብ በማድረግ እንደዚሁም የተተከሉ ችግኞችን በማረም ፣ በመኮትኮት እና በመንከባከብ ነው መርሐ ግብሩ እየተካሄደ ያለው።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል።

መርሐ ግብሩ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች ምቹ ፣ ፅዱ፣ ውብና ማራኪ እንዲሁም ሳቢ እንዲሆኑ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!