አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጳጉሜን 1 የበጎ ፈቃደኝነት ቀን እየተከበረ ይገኛል።
አዲሱን ዓመት 2015ን ለስኬት ያበቁንን ተሞክሮዎች እና እሴቶቻችንን በማስፋት፣ የተጋረጡብንን ፈተናዎች በድል አድራጊነት ለመወጣት የሚያስችሉ መደላድሎችን በመፍጠር መላው ኢትዮጵያዊ እንደሚቀበል የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል።
በየደረጃው በሚገኙ የፌደራል ተቋማት እንዲሁም በክልሎች በዚሁ ላይ ያተኮሩ ተግባራት እንደሚያከናውኑም ነው የተመለከተው።
ሀገራዊ ስኬቶችን ስንቅ በማድረግ ሁሉም ዜጋ በአዲሱ ዓመት ለአዲስ ድል እንዲነሳም ፅህፈት ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።
ጳጉሜን በመደመር በሚል መሪ ቃል ዛሬ ጳጉሜን 1 የበጎ ፈቃደኝነት ቀን ሆኖ በመከበር ላይ ይገኛል።
ጳጉሜን 2 የአምራችነት ቀን፣ ጳጉሜን 3 የሰላም ቀን፣ ጳጉሜን 4 የአገልጋይነት ቀን እና ጳጉሜን 5 የአንድነት ቀን ሆኖው ይከበራሉ።