የሀገር ውስጥ ዜና

ከመስከረም የመጀመሪያው አሥር ቀናት ጀምሮ የወቅቱ ዝናብ እየቀነሰ ይሄዳል – ኢኒስቲትዩቱ

By Feven Bishaw

September 05, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወቅቱ ዝናብ በብዙ የሀገሪቱ ክፍሎች ከመስከረም የመጀመሪያው አሥር ቀናት ጀምሮ እየቀነሰ እንደሚሄድ የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢኒስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ኢኒስቲትዩቱ የወቅቱ ዝናብ ሰጭ የሚቲዮሮሎጂ ገጽታዎች ከመስከረም ከመጀመሪያው አሥር ቀናት ጀምሮ ከሰሜን ምሥራቅና ከሰሜን ኢትዮጵያ ቀስ በቀስ እየተዳከመ ወደ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው ገልጿል፡፡