Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በብሪታንያ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ነገ ይታወቃል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪታንያ ወግ አጥባቂ ፓርቲ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆነውን አዲስ መሪውን በነገው ዕለት ይመርጣል።

የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በጫና ምክንያት የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም 11 እጩዎች ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት ሲፎካከሩ ቆይተው ሁለት የመጨረሻ እጩዎች ቀርተዋል።

የሀገሪቱ ወግ አጥባቂ ፓርቲም ከሁለቱ እጩዎች አንዳቸውን መሪ አድርጎ እንደሚመርጥ ቢቢሲ እና ሬውተርስ በዘገባቸው አመላክተዋል።

ሊዝ ትሩስ እና ሪሺ ሱናክም ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት የመጨረሻ እጩ ሆነው የቀረቡ ሲሆን፥ ሊዝ ትሩስ የተሻለ ድጋፍና ተቀባይነት አላቸው እየተባለ ነው።

እጩ ተወዳዳሪዋ የኃይል ዋጋ ማስተካከልን ጨምሮ የግብር ቅነሳ እና ሌሎችንም ማሻሻያዎች እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

ይህን እቅዳቸውን ለመተግበር ግን ጊዜ እፈልጋለሁም ብለዋል።

ሪሺ ሱናክም በኃይል ዋጋ ላይ ማስተካከያዎችን እንደሚያደርጉና በዋናነትም ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ገቢ ያላቸውን እና ጡረተኞችን የሚደጉም አሰራር እንደሚተገብሩ ገልጸዋል።

ፓርቲው በሚስጢራዊ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ሲሆን፥ ይህም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል።

Exit mobile version