Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዓይኔአበባ ንጉሥ የ”ፋና ላምሮት” የምዕራፍ አስራ አንድ ውድድር አሸናፊ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ፣ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓይኔአበባ ንጉሥ የ”ፋና ላምሮት” የምዕራፍ አስራ አንድ ውድድር አሸናፊ ሆናለች፡፡

የ”ፋና ላምሮት” የምዕራፍ አስራአንድ የባለተሰጥዖ ድምፃውያን ውድድር በዛሬው እለት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

ዛሬን ጨምሮ ለዘጠኝ ሣምንታት ሲካሄድ በቆየው የ“ፋና ላምሮት” የድምፃውያን ውድድር ፣ ተወዳዳሪዎች ራሳቸው በመረጧቸው እና ዳኞች በመረጡላቸው ሙዚቃዎች ሲፈተኑ መቆየታቸው ይታወቃል።

“ፋና ላምሮት” በቀጥታ ስርጭት ሲካሄድ ከዳኞች ሙያዊ ዳኝነት በተጨማሪ ተመልካቾችም በ”8222” ላይ የተወዳዳሪዎችን ኮድ በመላክ ሲደግፉ መቆየታቸው ይታወሳል።

በዛሬው የባለተሰጥዖ ድምፃውያን ውድድር ላይም አድማጭ ተመልካቾች እንደቀደመው ሁሉ ያልተገደበ የ”ኤስ ኤም ኤስ መልዕክቶቻቸውን” በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ኮድ በመላክ ይገባዋል ለሚሉት ተወዳዳሪ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፡፡

በዚህም በምዕራፍ አስራ አንድ የ”ፋና ላምሮት” የባለተሰጥዖ ድምፃውያን ውድድር የዓይኔአበባ ንጉሥ አንደኛ በመውጣት የ200 ሺህ ብር ፣ አሰግድ ስለሺ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ 150 ሺህ ብር ፣ ኤደን ገብረትንሳዔ ሶስተኛ በመውጣት 100 ሺህ ብር እንዲሁም አይተነው አቡኔ አራተኛ ደረጃ በመያዝ የ50 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version