Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመዲናዋ አስተዳደር የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት እርምጃ እየወሰድኩ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ፣ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር መጪዎቹን በዓላት ምክንያት በማድረግ የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋትና በአቅርቦትና ፍላጎት መሃከል የሚፈጠረውን ክፍተት ለማስተካከል እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

በዚህም መሠረት የዋጋ ማረጋጋት ግብረ ኃይል ተደራጅቶ ወደ ሥራ መግባቱን ነው ያስታወቀው፡፡

በቂ አቅርቦት ለከተማዋ እንዲኖር እና የዋጋ ንረት እንዳይፈጠርም ክትትልና ሕግ የማስከበር ሥራዎችን የሚያከናውን መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከአጎራባች አካባቢዎች በርካታ መጠን ያለው ምርት ወደ ከተማዋ መግባት መጀመሩንም አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

ለተከታታይ ቀናትም በእሁድ ገበያና የሸማች ማህበራት በስፋት የሰብል ምርቶችንና የተለያዩ አትክልት እና የእንስሳት ውጤቶች ለህብረተሰቡ በየአካባቢው እየቀረበ ነው መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ስለሆነም ህብረተሰቡ ምርቶቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ተጠቃሚ እንዲሆን ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Exit mobile version