Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በዲቦራ ፋውንዴሽን የተገነባውን መዋዕለ ህጻናት መረቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ፣ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በዲቦራ ፋውንዴሽን የተገነባውን መዋዕለ ህጻናት በዛሬው ዕለት መርቀዋል፡፡
በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነባው መዋዕለ ህጻናቱ፥ ዘጠኝ የመማሪያ ክፍሎች እና ሌሎች የአስተዳደር ቢሮዎች ያሉት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በምረቃ መርሐ ግብሩ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ም/ሃላፊ ወ/ሮ መገርቱ መሃመድ፣ የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በሪሶ ተመስገን እና የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራችና የቦርድ ሊቀ መንበር አቶ አባዱላ ገመዳ ተገኝተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ህጻናት የቤተሰብና የሀገር ተስፋ በመሆናቸው ህጻናቱ የትምህርትና የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ሁሉም ድጋፍ ሊያደርግላቸው ይገባል ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version