አዲስ አበባ፣ ነሐሴ፣ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ ለተፈናቀሉ ዜጎች የተዘጋጀውን የመኖሪያ መንደር በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡
በጋሞ ዞን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ባጋጠመ የመሬት ናዳ እና የጎርፍ አደጋ ምክንያት የ37 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ÷ ከ2 ሺህ 91 በላይ ሰዎች ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡
በዚህ ችግር የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍም በዞኑ ቁጫ ወረዳ ዳና ቀበሌ የተገነቡ 221 ቤቶች በዛሬው ዕለት በርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ መመረቃቸው ተገልጿል፡፡
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የደቡብ ክልል እና የጋሞ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!