Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከሳዑዲ ዓረቢያ መጥቶ ወደ ለይቶ ማቆያ ሊወሰድ ሲል ያመለጠው ግለሰብ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዚህ ቀደም ከሳዑዲ ዓረቢያ መጥቶ የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች አሳይቶ ወደ ለይቶ ማቆያ ሊወሰድ ሲል ያመለጠው ግለሰብ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ እንዳስታወቀው ግለሰቡ ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ በላቦራቶሪ ምርመራ ተረጋግጧል፡፡

ግለሰቡ ከአምቡላንስ አምልጦ ከሄደ በኋላ አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ በለጋምቦ ወረዳ መያዙ ይታወሳል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version