አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ለማፈራረስ በሙሉ አቅሙ ቆርጦ የተነሳው አሸባሪው ህወሓት በወልቃይት ግንባር በከፈተው ማጥቃት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት የሽብር ቡድኑ ምርኮኞች ተናገሩ።
ምርኮኞቹ ÷ አሸባሪው ህወሓት ያለንን አቅም ሁሉ ተጠቅመን ወልቃይትና ራያን አስመልሰን ታላቋን ትግራይ እንመሰርታለን ብሎ ጦርነት ውስጥ እንዳስገባቸው ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ የሽብር ቡድኑ ህወሓት ሃይል የቅዠት ህልሙን ሳያሳካ ሙት፣ ቁስለኛ እና ምርኮኛ ለመሆን መገደዱን ነው ምርኮኞቹ የተናገሩት፡፡
የሽብር ቡድኑ ህወሓት የትግራይ ወጣቶችና ታዳጊዎችን አስገድዶ በየግንባሩ ለጦርነት በመማገድ ላይ እንደሚገኝ መግለጻቸውንም ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡