አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት የኢትዮጵያን ብሄራዊ አንድነትና ጥቅም ከማይፈልጉ ባዕዳን ለሚሰጠው ተልዕኮ የሚያድር ጉዳይ አስፈፃሚ ነው ሲሉ ምሁራን ገለጹ፡፡
ምሁራኑ ኢትዮጵያ በአባይ ውሃ የመልማት ተፈጥሯዊ መብቷን እንዳትጠቀም የሚፈልጉ ባዕዳን የህወሓት ሽርክ መሆናቸውን አክለዋል።
ቡድኑ በትግራይ ህዝብ ስም እየቆመረ ህዝቡን ለመከራ መዳረጉን ያነሱት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጥናት ተመራማሪው ንጋቱ አበበ፥ ህወሓት ከሰላም ይልቅ ከባዕዳን በደረሰው ትዕዛዝ ጦርነት መጀመሩን አንስተዋል፡፡
ሰብዓዊ እርዳታን ለጦርነት በማዋልም ጸረ ህዝብነቱን አሳይቷልም ነው የሚሉት።
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ሴኔሳ ደምሴ በበኩላቸው፥ የህወሓት ተልዕኮ ኢትዮጵያን የማፍረስና ብሔራዊ ጥቅሟን አደጋ ላይ መጣል ነው ብለዋል።
የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን በማወክ ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማሳካት የሚፈልጉ ሃይሎች ህወሓትን በተላላኪነት እንደሚጠቀሙም ነው የተናገሩት።
እነዚህ ባዕዳን ኢትዮጵያ ውስጥ የብሔር፣ የሃይማኖትና ሌሎች ግጭቶችን ለማስነሳት እንደሚሰሩም ምሁራኑ አክለዋል፡፡
ምሁራኑ፥ ቡድኑ የጥፋት መንገዱን መቀጠሉ ጸረ ህዝብነቱን የገለጠ፣ ፀረ ህዝብነቱን ያሳየ እና ኢትዮጵያን ማህበራዊ እረፍት ለመንሳት ያለመ መሆኑን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ አንስተዋል ፡፡
ከቡድኑ ጎን ያሉት ሃይሎችም የኢትየጵያን እድገትና ብልጽግና የማይፈልጉ በድህነት እንድትኖር የሚሹ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ይህንን የሽብር ቡድንን ህወሓት ዘርፈ ብዙ ጥፋት ለማስቆምም ኢትዮጵያውያን በአንድነት እና በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ምሁራኑ አሳስበዋል።
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግና