አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጭው ጥቅምት ወር በዱባይ በሚካሄደው በዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ዐውደ ርዕይ በቢዝንስ አውትሶርሲንግ ሥራ የተሰማሩ አምስት የኢትዮጵያ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በዱባይ በሚካሄደው የጂአይቴክስ ግሎባል ጉባዔ የሚሳተፉት ኩባንያዎች÷ አፍሪኮም ቴክኖሎጂዎች፣ ኤክስለረንት ቴክኖሎጂ ሶሊውሽንስ፣ አይ ኔትወርክ ሶሊውሽንስ፣ ኦርቢት ሄልዝ ሶሊውሽንስ እና አር ኤንዲ ዲ ግሩፕ ናቸው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ ኩባንያዎቹ የሚሳተፉት ራሳቸውን ለማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን እምቅ አቅም ለሌሎች ለማስተዋወቅ መሆኑን ተገንዝበው ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ አለባቸው፡፡
ኩባንያዎቹ የተመረጡት የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት መሆኑም ተገልጿል፡፡
የቢዝንስ አውትሶርሲንግ ሥራ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቲጂ ልዩ ትኩረት የተሰጠው ዘርፍ መሆኑን ጠቁመው÷ ኩባንያዎቹ ለሚያደርጉት ዝግጅት ተገቢው ድጋፍ ይደረግላቸዋል ብለዋል፡፡
በዐውደ ርዕዩ÷ ከ100 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ ጎብኝዎች፣ ከ 4 ሺህ በላይ የቴክኖሎጂ መሪዎች እና 170 ሀገራት እንደሚሳተፉ የሚኒስቴሩ መረጃ ጠቁሟል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!