Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አይ ኤም ኤፍ ለዛምቢያ የ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ብድር አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ለዛምቢያ የ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ብድር አፀደቀ።
ተቋሙ በዛምቢያ ለዓመታት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የተመራበት መንገድ ችግር እንደነበረበት ጠቁማል።
የኢኮኖሚዋ ዕድገት መጠን ድህነትን ፣ የገቢ አለመመጣጠን እና የተመጣጠነ ምግብ እጦት ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል እንዳልነበረም ነው ያመለከተው።
የብድር ገንዘቡ የዛምቢያን ኢኮኖሚ ለማረጋጋት፣ ከፍተኛ እና የበለጠ አካታች እድገትን ለማምጣት እንደሚያግዝ ተቋሙ ተናግሯል።
ለአይ ኤም ኤፍ ብድር በምላሹ ዛምቢያ ሙስናን የመዋጋት፣ በነዳጅ ምርት ላይ የምታደርገውን ድጎማ መቀነስ እና ለግብርና ዘርፍ የምታውለውን ድጎማ ውጤታማነት ማሳገድ እንደሚጠበቅባት የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version