ኮሮናቫይረስ

መንገደኞች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄ

By Tibebu Kebede

March 16, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተሽከርካሪዎች ወደ ተለያዩ ቦታዎች የሚንቀሳቀሱ መንገደኞች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ቢያደርጉ ይመከራል።

  1. የተሽከርካሪ መስኮቶች ወይም መስታዎቶች በአግባቡ መከፈታቸውን ማረጋገጥ፣
  2. በጉዞም ሆነ ያለጉዞ የተሽከርካሪ መስኮቶችን እና መስታዎቶችን ሙሉ ለሙሉ መክፈት፣
  3. በህግ ከተፈቀደ የመጫን አቅም በላይ በዝቶና ተጨናንቆ አለመጫን፣
  4. በተሸከርካሪ ውስጥ አክታን እና የተጠቀሙበትን ሶፍቶች እና መሃረቦችን (ጨርቆችን) አለመጣል፣
  5. በተቻለ መጠን መስኮቶችን እና በሮችን ለመክፈት እንዲሁም በእጅ የሚያዙ የተሽከርካሪ ቦታዎችን ሲይዙ ጓንት፣ ጨርቅና ሶፍት መጠቀም፣
  6. የትራንስፖርት ክፍያ የገንዘብ ልውውጥ በተቻለ መጠን በጓንት በመጠቀም መለዋወጥ ወይም በእጆት የተለዋወጡ ከሆነ በውሃና በሳሙና ሳይታጠቡ ፊትን፣ አፍንጫን እና አፍን አለመንካት እና ምግብን አለመመገብ፣

ቫይረሱን ሪፖርት ወዳዳረጉ ሀገራት ሄዶ የቫይረሱን ምልክቶች ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቋም እንዲያሳውቅ ወይም ከታች በተገለፁት አድራሻዎች በመጠቀም ሪፖርት ያድርጉ።

  1. በነፃ የስልክ መስመር- 8335
  2. በመደበኛ የስልክ ቁጥር -0118276796
  3. በኢሜል አድራሻ ephieoc@gmail.com