አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤና ሚኒስቴር የወባ በሽታ የህብረተሰብ የጤና ችግር ወደማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በወባ በሽታ መከላከልና ጨርሶ በማጥፋት ላይ የሚሠሩ አካላት የምክክር መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሚኒስቴሩ በአገር አቀፍ ደረጃ ወባን ለማጥፋትና የህብረተሰብ የጤና ችግር ወደማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሠራ ነው፡፡
ወባን ጨርሶ ለማጥፋትም ሁሉም አካላት በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመው÷ ምርጥ ልምዶችን ማስፋት እና ደካማ አፈጻጸም በታየባቸው አካባቢዎች ደግሞ በትኩረት መሥራት ይገባል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ÷ በበሽታ ተህዋስያን፣ በምርመራና መከላከል ዘዴዎች፣ በበሽታ አስተላለፊ ትንኞች ባህርይና የፕሮግራም አፈጻጸም ላይ የምርምር ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!