የሀገር ውስጥ ዜና

የቡና ምርትና ጥራትን ለማሳደግ ለአርሶ አደሩ የሚደረገው እገዛ ይጠናከራል – አቶ ደስታ ሌዳሞ

By ዮሐንስ ደርበው

August 31, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡና ምርት እና ጥራትን ለማሳደግ ለአርሶ አደሩ የሚደረገው ሙያዊ እገዛ እንደሚጠናከር የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ተናገሩ፡፡

የሲዳማ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ የቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማቅመም ልማት ንቅናቄ መድረክ በሐዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡