የሀገር ውስጥ ዜና

የሐይማኖት መገናኛ ብዙሃን የጋራ እሴት እንዲጠናከርና አብሮነት እንዲጎለብት የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

By Shambel Mihret

August 31, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ተቋማት የጋራ እሴቶች እንዲጠናከሩ፣ አብሮነት እና ወንድማማችነት እንዲጎለብት የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በመተባበር “የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ለአብሮነት እሴቶች መጠናከር” በሚል መሪ ሀሳብ ከሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ጋር የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው፡፡

የውይይት መድረኩ ዓላማ የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን የሚያሰራጯቸው ይዘቶች በኢትዮጵያ ተከብሮ የቆየውን የሐይማኖት መቻቻልና አብሮነት ለማጠናከር እንዲሁም በሰላም እሴት ግንባታ ላይ ተገቢውን ሚና እንዲጫወቱ ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ እንደገለጹት÷ የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ግብረ ገብነትን በማስተማር ትውልድን ከማነፅ በተጨማሪ የጋራ እሴቶች እንዲጠናከሩ፣ አብሮነት እና ወንድማማችነት እንዲጎለብት የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን በአስተምህሮታቸው ለችግሮች መፍትሄ በሚያመጡ፣ ሀገር በሚገነቡና መልካም ዜጋን በሚያንፁ ጉዳዮች ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ማለታቸውን ከመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!