የሀገር ውስጥ ዜና

ዓለም አቀፍ ተቋማት የህወሓትን ዝርፊያ ማጋለጣቸው ለኢትዮጵያ ትልቅ የዲፕሎማሲ በር ይከፍታል -ፖለቲከኞች

By Feven Bishaw

August 31, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ ተቋማት የህወሓትን ዝርፊያ ማጋለጣቸው ለኢትዮጵያ ትልቅ የዲፕሎማሲ በር የሚከፍት መሆኑን ፖለቲከኞች ተናገሩ፡፡

ፖለቲከኞቹ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ ድርጊቱ ህወሓት ቆሜለታለሁ ለሚለው ህዝብ እንኳን ጭካኔው እስከምን ድረስ እንደሆነ አስረጂ ነው ብለዋል።