Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሚካኤል ጎርቫቾቭ አረፉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የሶቪየት ህብረት መሪ ሚካኤል ጎሮቫቾቭ አረፉ።
 
በ91 ዓመታቸው ያረፉት ጎርቫቸው፥ ለሞታቸው ምክንያት የሆነው ህመምን በተመለከተ የተገለፀ ነገር የለም።
 
ሆኖም ለረዥም ጎዜ በቆየ ህመም ምክንያት በተደጋጋሚ ወደ ሆስፒታል እየገቡ እንደነበር ተመልክቷል።
 
በአውሮፓውያኑ 1985 ዓመተ ምህረት ላይ የሶቪየት ኮሙዩኒስት ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ በቀጥታ የሶቪየት ህብረት መሪ ሆነዋል።
 
ምእራባውያን ቀዝቃዛውን የዓለም ጦርነት በሰላማዊ መንገድ በመቋጨት እና በተገበሯቸው ማሻሻያዎች ያሞካሿቸዋል።
 
ሆኖም የሶቪየት ህብረት እንዲፈራርስ አድርገዋል በሚል የሚወቅሷቸው ሩሲያውያን አያሌ ናቸው።
 
ጎርቫቸው የምስራቁ ዓለም እና የምዕራቡ ዓለም ግንኙነት እንዲሻሻል በማድረግ ላበረከቱት አስተዋፅኦ በፈረንጆቹ 1990 ላይ የኖቤል የሰላም ሽልማት ወስድዋል።
 
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጎርቫቾቭ ሞት ማዘናቸውን ገልፀዋል።
 
በርካታ የዓለም አገራት መሪዎችም ለጎርቫቸው ያላቸውን አድናቆት በመግለፅ የሀዘን መልዕክታቸውን በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ።
 
ጎርቫቸው፥ የቀብር ስነ ስርዓታቸው በሞስኮ ይፈፀማል ተብሏል።
Exit mobile version