የሀገር ውስጥ ዜና

የአሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል በዓል የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተከናወነ ነው

By Meseret Awoke

August 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በዓል የማጠቃለያ መርሐ ግብር በሚኒሊየም አዳራሽ እየተከናወነ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና በርካታ ታዳሚዎች ተገኝተዋል፡፡

ሴቶች በዚህ ማጠቃለያ መርሐ ግብር በባህል አልባሳት አጊጠው የተለያዩ ትርዒቶችን እያሳዩ ነው፡፡

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የተሰባሰቡ ብሄር ብሄረሰቦችም በዓሉን በአንድነት እያከበሩ መሆኑንም አስተያየታቸውን የሰጡ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

አሸንዳ ከነሐሴ 16 ቀን ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርአቶች ሲከበር ቆይቶ ዛሬ በአዲስ አበባ የማጠቃለያ መርሐ ግብሩ እየተከናወነ ነው፡፡

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ አዲስ አበባ የሁሉም ናት ፤ ዛሬም የአሸንዳ በአል ሲከበር የማህበረሰቡ እሴቶች ጎልተው የሚወጡበት ነው ብለዋል፡፡

አሸንዳ ሴቶች ሃሳባቸውን በነፃነት በመግለፅ የውስጣቸውን አቅም የሚያሳዩበት በዓል መሆኑን አንስተዋል፡፡

በሰዓዳ ጌታቸው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!