አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጳጉሜን 5 የሚከበረው “የአንድነት ቀን” በመላው ሀገሪቱና የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በሚገኙበት በታላቅ ድምቀት እንደሚከበር የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴው አስታወቀ፡፡
የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የመከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር ኮ/ል ጌትነት አዳነ፥ በዓሉ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበርና ተፈጥሯዊ የሆነውን ልዩነቶቻችን እንደ ችግር ለመጠቀም የሚፈልጉ የውጭና የውስጥ የሀገራችንን ጠላቶች በተለመደው ኢትዮጵያዊ አንድነታችን በመቆም ለዓለም የምናሳይበት በዓል ይሆናል ብለዋል።