Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጳጉሜን 5 የሚከበረው “የአንድነት ቀን” በመላው ሀገሪቱና በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ይከበራል – ኮሚቴው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጳጉሜን 5 የሚከበረው “የአንድነት ቀን” በመላው ሀገሪቱና የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በሚገኙበት በታላቅ ድምቀት እንደሚከበር የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴው አስታወቀ፡፡

የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የመከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር ኮ/ል ጌትነት አዳነ፥ በዓሉ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበርና ተፈጥሯዊ የሆነውን ልዩነቶቻችን እንደ ችግር ለመጠቀም የሚፈልጉ የውጭና የውስጥ የሀገራችንን ጠላቶች በተለመደው ኢትዮጵያዊ አንድነታችን በመቆም ለዓለም የምናሳይበት በዓል ይሆናል ብለዋል።

በዓሉ ከግለሰብ ጀምሮ በተለያዩ ተቋማት ደረጃ በታላቅ ድምቀት እንደሚከበርና አዲሱን ዓመት በአዲስ ተስፋ ለመቀበል የምንነሳሰበትና የአንድነት መገለጫ የሆነው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችንን የምናከብርበት ዕለት ይሆናልም ነው ያሉት።

የመንግስት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፥ በዓሉ ከኢትዮጵያ ውጭ በ52 የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ፅ/ቤቶች በድምቀት እንደሚከበር ገልፀዋል።

በዕለቱም ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎሉ የተለያዩ ዝግጅቶች ይደረጋሉ መባሉን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አምስት ሰዓት ላይ “እኔ ለሀገሬ አንድነት” የሚል ልዩ ፕሮግራም መሰናዳቱም ተጠቁሟል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version