የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአልጄሪያ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

By Melaku Gedif

August 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በአልጄሪያ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአልጄሪያ በነበራቸው ቆይታ÷ ከአገሪቱ ፕሬዚዳንት አብደልመጂድ ታቡን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም አልጀርስ የሰማዓታት መታሰቢያ ሙዚየምን እና ግዙፉን ሳይዳል የመድሃኒት ፋብሪካ መጎብኘታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡