Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሃይማኖት ለሰላም ክልል-አቀፍ ኮንፈረንስ በሐዋሳ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሃይማኖት ለሰላም” ክልል አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በሐዋሳ እየተካሄደ ነው።

የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መድረክ ከደቡብ፣ ሲዳማና ኦሮሚያ ክልሎች የተወከሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ የሥራ ኃላፊዎችና የሃይማኖት አባቶች እየተሳተፉበት ነው።

መድረኩ ሃይማኖታዊ እሴቶች ለሰላምና ለአብሮነት ያላቸውን ሚና ለማሳደግ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

በክልሎቹ አንዳንድ አካባቢዎች በተለያየ ጊዜ ያጋጠሙ የሰላም መደፍረስን ለመፍታት በተደረገው እንቀስቃሴ የሃይማኖት ተቋማት ሚናና ከመንግስት አካላት ጋር በነበራቸው ግንኙነት ላይ ውይይት ይደረጋልም ነው የተባለው።

የሃይማኖት ተቋማት ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ሂደት ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና ለማጉላትና ከመንግስት አካላት ጋር በመቀራረብ ለሰላምና ለአብሮነት እንዲሰሩ የሚያደርጉ ተመሳሳይ መድረኮች በቀጣይም በተለያዩ ክልሎች እንደሚካሄዱ ተገልጿል።

ለአንድ ቀን በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ሃይማኖት ለሰላም ባለው ሚና ላይ የተኮሩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ኢዜአ ዘግቧል።

በመድረኩም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለና የሰላም ሚኒስቴር ተወካይና የሰላም ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አወቀ አጥናፉን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version