አዲስ አበባ ፣መጋቢት 7፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት በአሜሪካ ሙከራ ሊደረግበት ነው።
በአሜሪካ ብሄራዊ የጤና ኢንስቲትዩት ፈንድ ድጋፍ የሚሰጠው ክትባት በዛሬው እለት ሲያትል በሚገኘው የጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ይሰጣል ተብሏል።
ክትባቱ ፈቃደኛ በሆኑ 45 ወጣቶች ላይ ይሞከራልም ነው የተባለው።፡
በአሜሪካ የህክምና ተመራማሪዎች የሚሰጠው ክትባት ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንደማያመጣም ተነግሯል፡፡
የክትባቱን አቅም ሙሉ በሙሉ ለማወቅ ከ12 እስከ 18 ወራት እንደሚወስድ ተገልጿል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቅርብ ቀናት ወዲህ ለቫይረሱ ክትባት እንዲፈለግለት ግፊት ማድረጋቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል።
ምንጭ፦ apnews.com/