ዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ።
የፕሬዜዳንታዊ ምርጫው የድምፅ ቆጠራ ከደቂቃዎች በፊት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በውጤቱም ላለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት የመሩት አቶ ኢሳያስ ጅራ 94 ድምፅ በማግኘት በድጋሚ ተመርጠዋል።
በእጩ ተወዳዳሪነት የቀረቡት አቶ መላኩ ፈንታ 27 ድምፅ ሲያገኙ አቶ ቶኪቻ ዓለማየሁ 17 ድምፅ ማግኘታቸውን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።