Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኦሮሚያ ክልል ከአማራና አፋር ህዝቦች ጎን በመሆን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር አስፈላጊውን መሰዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል እንደ ከዚህ ቀደሙ ከአማራና አፋር ህዝቦች ጎን ሆኖ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር አስፈላጊውን መሰዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን አረጋገጠቀ፡፡

ክልሉ በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ ያወጣ ሲሆን በመግለጫው፥ ከትናንት እስከ ዛሬ ይሄ አሸባሪ ቡድን ከታሪካዊ ጠላቶቻችን የተሰጠዉን ተልዕኮ እውን ለማድረግ ኢትዮጵያውያንን በብሔርና በሐይማኖት ከፋፍሎ ሲያባላ ኖሯል ነው ያለው።

ለዘመናት የኖርንበትን የመቻቻል እና ሃገራዊ አንድነታችንን ለመሸርሸር ያልፈነቀለው ድንጋይ እንደሌለም ጠቁሟል፡፡

ነገር ግን የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ስሪትና የህዝቦቿ አንድነት የተገመደበት እሴት የፍርሰት ሴራን ተቋቁሞ የቡድኑን የከፋፍለህ ግዛ ስርዓትን አሽቀንጥሮ በመጣል ነፃነት፣ እኩልነት፣ ወንድማማችነትና የህብረ ብሔራዊ አንድነት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር እውን እንዲሆን አድርጓል ብሏል፡፡

ኢ-ፍታዊነትና የበላይነትን የለመደው አሸባሪው ህወሓት እኩልነትን እንደ በደል በመቁጠር አሻፈረኝ በማለት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዖል ድረስ እንደሚጓዝ ግልፅ በማድረግ ባንዳነቱን አረጋግጧል ብሏል መግለጫው፡፡

ከግጭትና ጦርነት ውጪ መኖር የማይችለው አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ መንግሥት የተዘረጋለትን የሰላም እጅ አሻፈረኝ በማለት በአማራና አፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታ ላይ እየፈፀመ ያለውን ወረራ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በፅኑ ያወግዛል፤ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከአማራና አፋር ህዝቦች ጎን ሆኖ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር አስፈላጊውን መሰዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁነቱን ያረጋግጣል ብሏል በመግለጫው፡፡

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ!

………………….
አሸባሪው ህወሓት የኢትዮጵያን ሃገረ ምንግስት ስልጣን ተቆናጦ በነበረበት ዘመን፣ የአገራችን አንድነት ለመናድና ህዝቦቿን እርስ በርስ ለማናከስ ያልዘራው ጥላቻ፣ ያልሸረበው ሴራ አልነበረም፡፡

ከትናንት እስከ ዛሬ ይሄ አሸባሪ ቡድን ከታሪካዊ ጠላቶቻችን የተሰጠዉን ተልዕኮ እውን ለማድረግ ኢትዮጵያውያንን በብሔርና በሐይማኖት ከፋፍሎ ሲያባላ ኖሯል፡፡ ለዘመናት የኖርንበትን የመቻቻል እና ሃገራዊ አንድነታችንን ለመሸርሸር ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም።

መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ዘረፋዎችን አካሂዷል፣ ታሪክ ይቅር የማይለውን በደል በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ ፈፅሟል፡፡

ከምንም በላይ ደግም ሀገራዊ አንድነትን ለመናድ ያመቸዉ ዘንድ ሆን ብሎ የታዛቡ ታሪካዊ ኩነቶችን በመድረስ እና በመተረከ ኦሮሞና አማራን እሳትና ጭድ አድርጎ ሳለ፡፡

አንዱን ጠባብ ሌላውን ትምክህት ብሎ ሰየመ፡፡ እርስ በርስ በማናከስና ጥርጣሬን በማስፈን ከፋፍሎ መግዛትን የአገዛዙ ስልት አድርጎ ሲጠቀምበት ኖረ፡፡ ይሄም ብቻ ሳይሆን አሸባሪው ህወሓት በስልጣን ዘመኑ መባቻ ላይ ተዋልዶና ተጋምዶ ለዘመናት አብሮ የኖረውን የኦሮሞና የሶማሌ ህዝቦች አንድነት ለመናድ በሸረበዉ ሴራ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኦሮሞችን በማፈናቀል የጭካኔውን ጥግ አሳይቷል፤ የአገራችንን አንድነትም አደጋ ላይ ጥሎ ነበር፡፡

ነገር ግን የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ስሪትና የህዝቦቿ አንድነት የተገመደበት እሴት የፍርሰት ሴራን ተቋቁሞ የቡድኑን የከፋፍለህ ግዛ ስርዓትን አሽቀንጥሮ በመጣል ነፃነት፣ እኩልነት፣ ወንድማማችነትና የህብረብሔራዊ አንድነት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር እውን እንዲሆን አደረገ፡፡

ኢ-ፍታዊነትና የበላይነትን የለመደው አሸባሪው ህወሓት እኩልነትን እንደ በደል በመቁጠር አሻፈረኝ በማለት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዖል ድረስ እንደሚጓዝ ግልፅ በማድረግ ባንዳነቱን አረጋገጠ፡፡

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አጀንዳን እውን ለማድረግ በአማራና አፋር ክልሎች ቀጥተኛ ጥቃት በመፈፀም የንፁሃን ዜጎቻችን ደም አፍስሷል፣ ንብረት አውድሟል፤ የትግራይ ወጣቶችን በእሳት ማግዷል፡፡ በምስራቅ ኢትዮጵያ በኩል ከአልሸባብ ጋር በመሆን፣ በኦሮሚያ ክልል በአምሳሉ የፈጠረውን ሸኔን በመጋለብ፣ በቤንሻንጉልና በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ ምንግስታት ጭፍሮቹን በማሰማራት ኢትዮጵያን እረፍት ነስቶ በሂደት ለማፍረስ ያላደረገው ጥረት አልነበረም፡፡

ከግጭትና ጦርነት ውጪ መኖር የማይችለው አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ መንግሥት የተዘረጋለትን የሰላም እጅ አሻፈረኝ በማለት በአማራና አፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታ ላይ እየፈፀመ ያለውን ወረራ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በፅኑ ያወግዛል፤ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከአማራና አፋር ህዝቦች ጎን ሆኖ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር አስፈላጊውን መሰዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁነቱን ያረጋግጣል፡፡

አለማቀፉ ማህበረሰብም አሸባሪው ቡድን ህዝባዊ መዓበልን እንደወታደራዊ ስልት በመጠቀም እየፈፀመ ያለውን አስነዋሪና አረመኔያዊ ድርጊትን ማውገዝ ብቻ ሳይሆን ቡድኑ የኢትዮጵያ መንግስት የዘረጋውን የሰላም አማራጭ እንዲቀበል አስፈላጊውን ግፊት ማሳደር አለበት፡፡

አሸባሪው ህወሓት አሁን እየተከተለ ያለዉ ኋላቀር ህዝባዊ ማዕበልን እንደ ወታደራዊ ስልት በመጠቀም የትግራይ ወጣቶችን ለመማገድ ቆሮጦ መነሳቱን ያረጋጋግጣል።

ይህ ቡድን በዚህ ጭካኔ በተሞላበት ተግባር የጀመረዉን መጠነ ሰፊ ማጥቃት ካላቆመ አልያም ለተሰጠው የሰላም አማራጭ ይሁንታን ካላሳያ ለዜጎች ደህንነት፣ ለሀገራዊ ሉዓላዊነት እና አንድነት ሲባል የፌደራል መንግስት የሚወሰደዉን ህጋዊና ሞራላዊ እርምጃዎችን በፅኑ የሚደግፍ መሆኑን የኦሮሚያ ብሐራዊ ክልላዊ መንግስት ያረጋግጣል።

ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ነሐሴ 22, 2014

Exit mobile version