Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ የክብር ዶክትሬት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ሰጠ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ የክብር ዶክትሬቱን የሰጣቸው÷ በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር እየኖሩ ያሉ እንዲሁም ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚያከብሩ ታላቅ ዓርዓያ ሰብ በመሆናቸው ነው ብሏል፡፡

እንዲሁም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ÷ በአትሌቲክስ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ፋና ወጊ አትሌት እና ለህብረሰተብ ፍቅርና አንድነት መጎልበት እየተጋች ያለች የኢትዮጵያዊነት ተምሳሌት በመሆኗ ዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክትሬት ሰጥቷታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version