የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 66 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ

By Shambel Mihret

August 26, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ 1 ሺህ 66 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻላቸው ተገለፀ፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 1 ሺህ 54ቱ ወንዶች ሲሆኑ፥ 12ቱ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጁላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ 70 ሺህ 749 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!