የሀገር ውስጥ ዜና

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

By Shambel Mihret

August 26, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዓመት የምርጫ ጊዜ አንደኛ የስራ ዘመን መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በጉባዔው በ2014 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ያደርጋልም ተብሏል፡፡

ጉባዔው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ በክልሉ የዞን አደረጃጀት ለማቋቋም የወጡና ሌሎች አዋጆችን ለምክር ቤቱ አቅርቦ ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል።

በተጨማሪም የ2015 በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቦ ይጸድቃል ተብሏል፡፡

ባለፉት አራት ቀናት የምክር ቤት አባላት በ2014 ዓ.ም ላይ የተሰሩ የልማት ሥራዎችን በመጎብኘት ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸውም ተገልጿል፡፡

በታመነ አረጋ ፣ መቅደስ አስፋውና ብርሃኑ በጋሻው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!